በካናዳ ተወልደው ላደጉ የአብነት ተማሪዎች ሢመተ ዲቁና ተሰጠ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምዕራብ ካናድ ሀገረ ስብከት ኤድመንተን በሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም አጥቢያ ቤተክርስቲያን ተወልደው ላደጉ 9 የአብነት ተማሪዎች ዲቁና ተሰጠ። ለ ዓመታት የአብነት ትምህርታቸውን ሲከተታሉ ለነበሩት ዘጠኝ አዳጊ የአብነት ተማሪዎች ነሐሴ 20 ቀን 20115 ዓ.ም. በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብጹዕ አቡነ አብርሃም ማዕርገ ዲቁና ተሰጥቷል፡፡
የደብራችን ካህናት በተለየም ደግሞ መርጌታ ይኋንስ የአብነት የአብነት ትምህርቱንም በመከታተል በማስተማር፤ ተተኪው ትውልድ በትክክል እንዲቀረጽ እና የነገዋ ቤተ ክርስቲያን ተረካቢ እንዲሆን፣ በደብሩ የሚገኙት አዳጊ ወጣቶችም በፈሪሃ እግዚአብሔር፣ በፍቅረ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንዲያድጉና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ እንዲያውቋት በማድረግ ረገድ፡ በአጥቢያው የሚገኙትን ማኅበረ ምእመናን በማስተባበር አባታዊ ሓላፊነታቸውን በመወጣት ላይ ይገኛሉ፡፡
በአሁኑ ጊዜ በደብሩ ከሰባ በላይ ተማሪዎች የአብነት ትምህርትን ለማስተማር ከመስከረም ጀምሮ ለየት ባለ መልኩ ለወደፊት ዲ/ናት እንዲሁም ለሕጻናት እና ወጣት ሴቶችን መዝሙረ ዳዊት እንዲሁም ውዳሴ ማርያም ለማጨረስ አባቶች ካህናት ሰፊ ዝግጅት አድርገው የትምህርቱን መከፈት በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡

image (13)
image (12)
image (11)
image (10)
image (9)
image (8)
image (7)
image (6)
image (5)
image (4)
image (3)
image (2)
image (1)
previous arrow
next arrow